ማስታወቂያ ለትምህርት ፈላጊዎች
የደ/ብርሃን ቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከቅዱስ ሲኖዶስ በተሰጠው ሙሉ እውቅና መሠረት ከመደበኛው የመማር ማስተማር በተጨማሪ በ 2018 ዓ/ም የቲኦሎጂ ትምህርት ፈላጊዎችን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት ዘርፎች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተማሪዎችን በዕረፍት ቀናት በኤክስቴንሽን መርሐ ግብር ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።
በመሆኑም ትምህርት የሚሰጥባቸው መርሐ ግብሮች፦
በነገረ መለኮት (Theology) በዲፕሎማ
በካህናት ልዩ ዲፕሎማ /ሴሚናሪ/
በነገረ መለኮት ዲፕሎማ የመግቢያ መስፈርት፦
ሀ/ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ ውጤቱ ከ 200 እና ከዚያ በላይ
ለ/ በድሮው 10ኛ ክፍል ያጠናቀቀና ወይም 10+2 ያለው /ላት/ ከ 2 ነጥብ በላይ ያለው/ላት/ ወይም ደረጃ 3 እና 4 በቴክኒክ እና ሙያ ሰርተፍኬት የተመረቀ/ች/
ለካህናት ልዩ ዲፕሎማ (ሴሚናሪ) መግቢያ መስፈርት፦
1. ቄስ ወይም መነኩሴ የሆነ ወይም ድቁና ያለው፤
2. መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የተማረ፤
3. ከሚያገለግልበት ደብር ወይም አጥቢያ ሠራተኛ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤
ለሁሉም ትምህርት ፈላጊዎች በምዝገባ ወቅት ይዘው መቅረብ ያለባቸው፦
የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃና ከሚያገለግሉበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ማረጋገጫ ደብዳቤ፤
የትምህርት ማስረጃዎች ኦርጅናሉንና የማይመለስ ኮፒ በመያዝ፤
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 10/2018 ዓ።ም ድረስ በኮሌጁ ቢሮ ቁጥር 3 በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።
ክፍያን በተመለከተ
የማመልከቻ፡ የመጀመሪያ መመዝገቢያ 200 ብር፤
ለሴሚስተር ምዝገባ፡ ለቲኦሎጂ ዲፕሎማ 100 ብር፤
ለካህናት ልዩ ዲፕሎማ 100 ብር፤
የክሬዲት ሀዎር፡ 210 ብር
ማሳሰቢያ
በኮሌጁ የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና ያለፈ/ች/ ከላይ በተጠቀሰው መሰረት የሴሚስተር መመዝገቢያና የክሬዲት ሀወር ክፍያ ብር እና ሁለት ጉርድ ፎቶዎችን በማቅረብ በኮሌጁ ሬጅስትራር መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን።
የገንዘቡን ክፍያ በተመለከተ በአሐዱ ባንክ ደ/ብርሃን ቅርንጫፍ (አጅፕ) የባንክ ቁጥር 0078146811701 ገቢ አድርጋችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን።