Saint Basilios Theological College Logo
ቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ

ጽሑፍ እና ዜና

Theological journals, news updates, and research papers

NOTICE TO ALL APPLICANTS
ማስታዎቂያ 8/17/2026

ማስታወቂያ ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን የደብረ ብርሃን ቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በ2019 ዓ/ም የቲኦሎጂ ትምህርት ፈላጊዎችን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት ዘርፎች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተማሪዎችን በዕረፍት ጊዜ በኤክስቴንሽን መርሐ ግብር ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል። በመሆኑም ትምህርት የሚሰጥባቸው መርሐ ግብሮች፦ በነገረ መለኮት (Theology) በዲፕሎማ በካህናት ልዩ ዲፕሎማ /ሴሚናሪ/ በነገረ መለኮት ዲፕሎማ የመግቢያ መስፈርት፦ 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ ውጤቱ ከ200 እና ከዚያ በላይ ያለው። በቀድሞው 10ኛ ክፍል ያጠናቀቀና ወይም 10+2 ያለው /ላት/ ከ9 ነጥብ በላይ ያስመዘገበ። ወይም ደረጃ 3 እና 4 በቴክኒክና ሙያ ሰርተፍኬት ያለው /ያላት። በካህናት ልዩ ዲፕሎማ (ሴሚናሪ) መግቢያ መስፈርት፦ ቀሲስ ወይም መነኩሴ የሆነ ወይም ዲቁና ያለው። መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የተማረ፣ በአገልግሎት ላይ ያለ። ከሚያገለግልበት ደብር ወይም አጥቢያ ሠራተኛ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል። የሁሉም ትምህርት ፈላጊዎች በምዝገባ ወቅት ይዘው መቅረብ ያለባቸው፦ የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃና ከሚያገለግሉበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ማረጋጫ ደብዳቤ። የትምህርት ማስረጃዎች አርጅናሉንና የማይመለስ ኮፒ በመያዝ። ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 15/2019 ዓ/ም ድረስ በሸዋሮቢት ወረዳ ቤተክህነት ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ በሥራ ቀናት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን። ክፍያን በተመለከተ፦ ተ/ቁ የክፍያ ዓይነት ፕሮግራም የክፍያው መጠን 1 የማመልከቻ የነገረ መለኮት መርሐግብር 200 2 ሰበአጥቢያ ምዝገባ በነገረ መለኮት 100 በካህናት ልዩ ዲፕሎማ 100 3 የክሬዲት ሰዓት 210 ማሳሰቢያ በላይ የተጠቀሰውን የምዝገባ ክፍያ በማድረግ እና ሁለት ጉርድ ፎቶዎችን በማቅረብ በሸዋሮቢት ወረዳ ቤተክህነት ጽ/ቤት በሥራ ቀናት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን። የገቢውን ክፍያ በተመለከተ አዋሽ ባንክ ሸዋሮቢት ቅርንጫፍ የተከፈተ የባንክ ቁጥር 013521786545900 ገቢ አድርጋችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን።

Debre Berhan Saint Basilios Theological College to Launch Weekend Extension Program in Shewarobit for the 2019 E.C. Academic Year
ዜና 7/22/2026

የደብረ ብርሃን ቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በሸዋሮቢት ከተማ ትምህርት ሊጀምር መሆኑን አበሠረ።

ሐምሌ ፲፭ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም (አቡቀለምሲስ ሚዲያ ፤ ደብረ ብርሃን) የደብረ ብርሃን ቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሸዋሮቢት ከተማ ቅዳሜ እና እሁድ በኤክስቴንሽን ትምህርት ለማስተማር መዘጋጀቱን አብሥሯል። ይህ የምሥራች ይፋ የተደረገው የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮች ከሸዋሮቢትና ከቀወት ወረዳ ቤተ ክህነት የሥራ ሓላፊዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ባካሔዱት ውይይት መሆኑ ተገልጿል። በዕለቱ በስፋት ማብራሪያ የሰጡት የኮሌጁ አመራሮች፡-ዶክተር አቤሴሎም ነቅዐጥበብ፦የቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዋና ዲን፣ ሊቀ አእላፍ ዮርዳኖስ አቢ፦ የቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ምክትል ዲን፣ ሊቀ ልሳናት ደበበ ፍልቄ፦የቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ አካዳሚክ ዲን ናቸው። አመራሮቹ በገለጻቸው ኮሌጁ የሚያስተምራቸውን የትምህርት መስኮች እና የትምህርት አሰጣጥ ሂደቶችን አብራርተዋል። የውይይቱ ተሳታፊዎች ለአካባቢው ቅድሚያ በመስጠት ለተደረገላቸው መልካም እድል ለሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስን የላቀ ምስጋና አቅርበዋል። በተመሳሳይ ቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ አመራሮች ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፣ ለቀጣዩ የትምህርት ዘመን ስኬትም የድርሻቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል። በውይይቱ ላይ የሸዋሮቢት ከተማ ወረዳ ቤተ ክህነት፣ የቀወት ወረዳ ቤተ ክህነት እንዲሁም የአጎራባች ወረዳዎች ካህናት፣ ዲያቆናት፣ መዘምራን እና የሰንበት ትምህርት ቤት ተወካዮች ተሳትፈዋል ሲል የዘገበው ሸዋሮቢት ከተማ ቤተ ክህነቱ ሚዲያ ነው።

Debre Birhan Saint Basilios Theological College Reviews Its Five-Year Strategic Plan
ዜና 7/6/2026

ኮሌጁ የአምስት ዓመት ስትራቴጅካዊ ዕቅድ ክለሳ አደረገ።

የደብረ ብርሃን ቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የነበረውን የ5 ዓመት ስትራቴጅካዊ ዕቅድ ይዘትና አፈጻጸም ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር ያለመ የዕቅድ ክለሳ አድርጓል። የኮሌጁን የትምህርት ጥራት፣ የምርምር አቅምና የማኅበረሰብ አገልግሎት ተደራሽነት ይበልጥ ለማዘመን ታስቦ የተመደበው ይኸው የምሁራን የባለሙያዎች ቡድን (Team) የመጀመሪያውን ረቂቅ ሰነድ ግምገማ በኮሌጁ የቦርድ ጽሕፈት ቤት አካሒዷል። ይህ የስትራቴጅካዊ ዕቅድ ክለሳ ኮሚቴ የተዋቀረውና ሥራውን የጀመረው በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ አባታዊ መመሪያ ሰጪነትና የበላይ ጠባቂ መሆኑ ተመልክቷል። ክለሳው ተቋሙ በአገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የነባር መንፈሳዊና ዘመናዊ ዕውቀት ማዕከልነት ሚና ለማጠናከርና የዘመኑን ተለዋዋጭ ፍላጎቶች ለመዋጀት ትልቅ መሠረት እንደሚጥል ይጠበቃል። የተሰየመው የምሁራን ቡድን በስትራቴጅካዊ ዕቅዱ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት፣ ጠንካራ ጎኖችን በማጎልበትና አዳዲስ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ አሠራሮችን በማካተት ተቋማዊ ራእዩን ዳር የሚያደርስ የተሟላ ሰነድ በቅርቡ አጠናቆ ለቦርዱ እንደሚያቀርብም ተመላክቷል።