Saint Basilios Theological College Logo
ቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ
ማስታዎቂያ 8/17/2026 97 Views

ማስታወቂያ ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

A
Admin User Academic Contributor & Faculty
NOTICE TO ALL APPLICANTS

የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን የደብረ ብርሃን ቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በ2019 ዓ/ም የቲኦሎጂ ትምህርት ፈላጊዎችን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት ዘርፎች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተማሪዎችን በዕረፍት ጊዜ በኤክስቴንሽን መርሐ ግብር ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

በመሆኑም ትምህርት የሚሰጥባቸው መርሐ ግብሮች፦

  1. በነገረ መለኮት (Theology) በዲፕሎማ
  2. በካህናት ልዩ ዲፕሎማ /ሴሚናሪ/

በነገረ መለኮት ዲፕሎማ የመግቢያ መስፈርት፦

  1. 12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ ውጤቱ ከ200 እና ከዚያ በላይ ያለው።
  2. በቀድሞው 10ኛ ክፍል ያጠናቀቀና ወይም 10+2 ያለው /ላት/ ከ9 ነጥብ በላይ ያስመዘገበ።
  3. ወይም ደረጃ 3 እና 4 በቴክኒክና ሙያ ሰርተፍኬት ያለው /ያላት።

በካህናት ልዩ ዲፕሎማ (ሴሚናሪ) መግቢያ መስፈርት፦

  1. ቀሲስ ወይም መነኩሴ የሆነ ወይም ዲቁና ያለው።
  2. መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የተማረ፣ በአገልግሎት ላይ ያለ።
  3. ከሚያገለግልበት ደብር ወይም አጥቢያ ሠራተኛ መሆኑን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

የሁሉም ትምህርት ፈላጊዎች በምዝገባ ወቅት ይዘው መቅረብ ያለባቸው፦

  • የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያን እምነት ተከታይ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃና ከሚያገለግሉበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ማረጋጫ ደብዳቤ።
  • የትምህርት ማስረጃዎች አርጅናሉንና የማይመለስ ኮፒ በመያዝ።
  • ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 15/2019 ዓ/ም ድረስ በሸዋሮቢት ወረዳ ቤተክህነት ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ በሥራ ቀናት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።

ክፍያን በተመለከተ፦

ተ/ቁ የክፍያ ዓይነት ፕሮግራም የክፍያው መጠን
1 የማመልከቻ የነገረ መለኮት መርሐግብር 200
2 ሰበአጥቢያ ምዝገባ በነገረ መለኮት 100
በካህናት ልዩ ዲፕሎማ 100
3 የክሬዲት ሰዓት 210

ማሳሰቢያ

  • በላይ የተጠቀሰውን የምዝገባ ክፍያ በማድረግ እና ሁለት ጉርድ ፎቶዎችን በማቅረብ በሸዋሮቢት ወረዳ ቤተክህነት ጽ/ቤት በሥራ ቀናት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን።
  • የገቢውን ክፍያ በተመለከተ አዋሽ ባንክ ሸዋሮቢት ቅርንጫፍ የተከፈተ የባንክ ቁጥር 013521786545900 ገቢ አድርጋችሁ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳስባለን።

አስተያየቶች (0)

No comments published yet. Be the first to share your thoughts!

Submit a Comment