Saint Basilios Theological College Logo
ቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ
ዜና 7/6/2026 139 Views

ኮሌጁ የአምስት ዓመት ስትራቴጅካዊ ዕቅድ ክለሳ አደረገ።

A
Admin User Academic Contributor & Faculty
Debre Birhan Saint Basilios Theological College Reviews Its Five-Year Strategic Plan

የደብረ ብርሃን ቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የነበረውን የ5 ዓመት ስትራቴጅካዊ ዕቅድ ይዘትና አፈጻጸም ወደ ላቀ ምዕራፍ ለማሸጋገር ያለመ የዕቅድ ክለሳ አድርጓል። የኮሌጁን የትምህርት ጥራት፣ የምርምር አቅምና የማኅበረሰብ አገልግሎት ተደራሽነት ይበልጥ ለማዘመን ታስቦ የተመደበው ይኸው የምሁራን የባለሙያዎች ቡድን (Team) የመጀመሪያውን ረቂቅ ሰነድ ግምገማ በኮሌጁ የቦርድ ጽሕፈት ቤት አካሒዷል። ይህ የስትራቴጅካዊ ዕቅድ ክለሳ ኮሚቴ የተዋቀረውና ሥራውን የጀመረው በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ አባታዊ መመሪያ ሰጪነትና የበላይ ጠባቂ መሆኑ ተመልክቷል። ክለሳው ተቋሙ በአገር አቀፍና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የነባር መንፈሳዊና ዘመናዊ ዕውቀት ማዕከልነት ሚና ለማጠናከርና የዘመኑን ተለዋዋጭ ፍላጎቶች ለመዋጀት ትልቅ መሠረት እንደሚጥል ይጠበቃል። የተሰየመው የምሁራን ቡድን በስትራቴጅካዊ ዕቅዱ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት፣ ጠንካራ ጎኖችን በማጎልበትና አዳዲስ አገራዊና ዓለም አቀፋዊ አሠራሮችን በማካተት ተቋማዊ ራእዩን ዳር የሚያደርስ የተሟላ ሰነድ በቅርቡ አጠናቆ ለቦርዱ እንደሚያቀርብም ተመላክቷል።

አስተያየቶች (1)

tesfaye mebrate 9/14/2026

This is the very critical and timely decision of the EOTC, especially, the North Shewa Diocese (Debre Berhan) to strengthen our unique and eternal faith, i.e., Orthodoxy foundation. The collage is envisioned to fill major gaps of the EOTC which are chronic in these days.

Submit a Comment