Saint Basilios Theological College Logo
ቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ

ስለ እኛ

የኮሌጁን ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ እሴቶች፣ ዓላማዎች እና የወደፊት ዕቅድ በዝርዝር ያሳያል።

የደብረ ብርሃን ቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ

የደብረ ብርሃን ቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በባለራዕዩና አርቆ አሳቢው አባት በብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በመ/ፓ/ጠ/ጽ/ት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ፣ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ መሥራችና የኮሌጁ በላይ ኃላፊ ሐሳብ አመንጭነት በጥቅምት ወር 2016 በተደረገው የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ፍቃድ በማግኘቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል አንዱ በመሆን ከአዲስ አበባ በስተሰሜን ምስራቅ 130 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው በአጼ ዘርዓ ያዕቆብ (1426–1464) ዘመነ መንግሥት በተቆረቆረችው፣ የነገሥታቱ መናሃሪያና የሰሜን ሸዋ ዞን ርዕሰ ከተማ በሆነችው በደጋማዋ ገነት በደብረ ብርሃን ከተማ በ2016 ዓ.ም ተከፈተ፡፡


Abune Basilios Image

የደብረ ብርሃን ቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ስያሜውን ያገኘው በመጀመሪያው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ ኮሌጁ በነገረ መለኮት፣ በሕግ፣ በቱሪዝምና ቅርስ አስተዳደር ለመማር መሥፈርቱን የሚያሟሉ ደቀመዛሙርትን ከየአህገረ ስብከቱ ተቀብሎ በመደበኛና በተከታታይ ትምህርት እያስተማረ ይገኛል፡፡ በመሆኑ ኮሌጁ የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት ለቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ተጨማሪ ሊቃውንትን በማፍራት ረገድ የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግ በከፍተኛ ጥረት ላይ ይገኛል።


Abune Basilios Image

የኮሌጁ ራዕይ

የመንፈሳዊ ኮሌጁን ራዕይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያላት መንፈሳዊ አእምሮአዊና ቁሳዊ የሆኑ ዘርፈ ብዙ እውቀቶች በስፋትና በጥልቀት የሚጠኑበት፣ በመማር ማስተማርና በምርምር በኢትዮጵያ ከሚገኙ መንፈሳዊ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች በአፍሪካና በዓለም ታዋቂና ቀዳሚ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሆኖ ማየት፡፡

የኮሌጁ ተልዕኮ

የመንፈሳዊ ኮሌጁን ተልዕኮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ (ትምህርተ ሃይማኖት ፣ቀኖና፣ ትውፊትና ሥርዓተ አምልኮ) መሠረቱን ሳይለቅ ብሔራዊና ዓለማቀፋዊ ብቃት ያላቸውን የሥነ መለኮት፣ የቱሪዝምና ቅርስ አስተዳደር እንዲሁም የሕግ ምሁራንን የማፍራትና ጥራት ያለው ትምህርትና ስልጠና፣ ችግር ፈቺ ምርምር ማከናወን፣ ከመንፈሳዊ የትምህርት ተቋም የሚጠበቀውን መንፈሳዊና ማኅበራዊ አገልግሎት መስጠት፡፡

የኮሌጁ ዓላማዎች

• የመንፈሳዊ ኮሌጁን ራዕይ እውን የሚያደርጉ ተልእኮውን የሚያሳኩ ደቀመዛሙርት ከየአህጉረ ስብከቱን ተቀብሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት፣ ቀኖና፣ ትውፊትና ሥርዓተ አምልኮ እንዲሁም የተለያዩ ማኅበራዊና መንፈሳዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ተዛማጅ ትምህርቶች ዓለማቀፋዊ ጥራቱንና ደረጃውን በጠበቀ መንገድ በቅድመ ምረቃና ድኅረ ምረቃ መርሐ ግብር ማስተማር፡፡


• ዘመኑን የዋጁ በተዋሕዶ እምነት የጸኑ፣ በሥነ መለኮት፣ በሕግ፣ በቱሪዝምና ቅርስ አስተዳደር ትምህርቶች ጥልቅ እውቀት ያላቸውና በሁለተናዊ አገልግሎት ብቁ የሆኑ ሊቃውንትን ማፍራት፡፡


• ቤተ ክርስቲያንን በልዩ ልዩ ሙያ ዘርፍ በማገልገል ላይ ለሚገኙ ካህናትና ምእመናን ሙያቸውን እንዲያሳድጉ በተለያየ ደረጃ ትምህርት ስልጠና መስጠት፡፡


• ከመደበኛ የትምህርት መርሐ ግብር በተጨማሪ ካህናትንና ምእመናንን በተከታታ የትምህርት መርሐ ግብር በማስተማር ዘመኑን የዋጀ ጠንካራ ሐዋርያዊ አገልግሎት ማብቃት፡፡


• ቤተ ክርስቲያንኒቱ በነገረ መለኮት ትምህርት በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥራቱን የጠበቀና ሀገራዊ ፋይዳ ያለውን የአካዳሚክ ማኅበረሰብን በመፍጠር በአርአያነት ተጠቃሽ የሆነ ተግባራትን መፈፀም፡፡


• በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚነዙትን የርእዮተ ዓለም እንቅስቃሴ ጥናት እና ምርምር ላይ ተመርኩዞ መሞገት የቤተ ክርስቲያንን ሕልውና ማስጠበቅ፡፡ ስለቤተ ክርስቲያኒቱ ታሪክ፣ ትውፊት፣ ቅርስ፣ ሕግ ወዘተ. ማስተማርና ማሳወቅ፡፡


• ተገቢውን የመማር ማስተማር ሥርዓት በመዘርጋት ትኩረት በሚሹ በኦርቶዶክሳዊ ሥነ መለኮት፣ በቅርስና ቱሪዝም አስተዳደርና በሕግ ጉዳዮች ላይ ችግር ፈቺና ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ምርምሮችን ማካሄድና ማስረጽ፤


• የቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ በሀገር ውስጥ ከሚገኙ የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ኮሌጆች በዓለም አቀፍ ደረጃ ከኦሬንታል ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አኃት አብያተ ክርስቲያናት የትምህርት ተቋማት ጋር በትምህርት፣ በጥናትና ምርምር ግንኙነት መፍጠር፡፡


• ቤተ ክርስቲያን ያላትን ጥንታዊ የብራና መጻሕፍትን፣ ሌሎች ንዋየ ቅድሳት እንዲሁም የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች ለትምህርት፣ ለጥናትና ምርምር ማዋል፡፡


• መንፈሳዊ ኮሌጁ ዘመኑን የዋጀ ተቋማዊ የአሠራር ሥርዓት በመዘርጋት የመማር ማስተማር ተልእኮውን ለማሳካት የሚችልበት በሰው ኃይል፣ በመንፈሳዊነት፣ በማኅበራዊ ግንኙነት፣ በዕውቀት፣ በልማት፣ በፋይናንስ፣ በቴክኖሎጂ አቅም መፍጥር፡፡


• ኮሌጁ ካርኩለም ተቀርጾላቸው በሚሰጡ የትምህርትና ስልጠና መስኮች፣ እንዲሁም በአጫጭርና በረጅም ስልጠናዎች፣ በጥናትና ምርምር በሁለንተናዊ አፈጻጸሙ የእውነተኛውና መሠረቱን የጠበቀው ኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶ አስተምሕሮ የልሕቀት ማእከል ማድረግ፡፡

የኮሌጁ ዕሴቶች

እግዚአብሔርን መፍራት፤ የኦርቶዶክሳዊ ተዋሕዶ ቅዱሳን አባቶች ፈለግ መከተል፡፡

.

ጥራትና አግባብነት ያለው ትምህርት፣ የጥናትና ምርምር አገልግሎት፣ ተደራሽነት መፍትሄ አፍላቂነት፣ አእምሯዊ ብልጽግና፣ ዓለማቀፋዊ እይታን ማስፋት፡፡

.

ለመንፈሳዊ፣ ለማኅብራዊና ለሀገራዊ እንዲሁም ለአለም አቀፉዊ አገልግሎት ዝግጁ መሆን፤ እውቀትን ማጋራት፣

.

ዘመኑን መዋጀት፣ ፍትሐዊነት፣ ግልጸኝነት፣ ኃላፊነት፣ ተጠያቂነት፣ አሳታፊነት፣ አገልጋይነትን በማስፈን የኢ/ኦ/ተ/ቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትና ሕግ መጠበቅ፣

.

መልካም ስብእና እና ሥነ ምግባር መላበስ፤ ክርስቲያናዊ ግብረ ገብነትን፤ሰው መውደድን፣ ተአማኝነትን ትሑትነትን መንፈሳዊ ጥብዐትን መላበስ፡፡

.

ለመንፈሳዊ፣ ለማኅብራዊና ለአገራዊ እንዲሁም ለአለም አቀፉዊ አገልግሎት ዝግጁ መሆን፤ እውቀትን ማጋራት፣ ዘመናዊና ቀልጣፉ አሰራር መስጠት፡፡

.

ዘመኑን መዋጀት፣ ፍትሐዊነት፣ ግልጸኝነት ሃላፊነት፣ ተጠያቂነት፣ አሳታፊነት፣ አገልጋይነት የኮሌጁን ሕግና ደንብ ማክበር፡፡

.

ለአብነት ትምህርት (ሀገር በቀል እውቀት) ትኩረት መስጠት

.

የአካዳሚክ አመራር

Abune Basilios Image

ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ/በመ/ፓ/ጠ/ጽ/ት የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማደራጃ መምሪያ፣ የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ባስልዮስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ



አቤሴሎም ነቃጥበብ, (BTH, MA, MA, Ph.D.)

የቅዱስ ባሲልዮስ ሥነ መለኮት ኮሌጅ ዲን

Abune Kelemnitos

ሊቀ ሊቃውንት ደበበ ፍልቄ (BTH, MBA)

የቅዱስ ባሲልዮስ ሥነ መለኮት ኮሌጅ አካዳሚክ ምክትል ዲን

Abune Kelemnitos

ሊቀ አንስት ዮርዳኖስ አቢ (BTH, MBA)

የቅዱስ ባሲልዮስ ሥነ መለኮት ኮሌጅ አስተዳደራዊ ምክትል ዲን

Abune Kelemnitos

መ/ር ሰሎሞን ልዑል (BTH, MTM)

የቅዱስ ባሲልዮስ ሥነ መለኮት ኮሌጅ የተማሪዎች ጉዳይ ኃላፊ

Abune Kelemnitos

መ/ር እያሱ ገረመው (BTH, MTM)

የቅዱስ ባሲልዮስ ሥነ መለኮት ኮሌጅ ሬጅስትራር ኃላፊ

የኮሌጁ ቀጣይ አቅጣጫ

ኮሌጁ የመማር ማስተማሩን ሥራ ለማስፋፋትና ተጨማሪ የትምህርት ክፍሎችን ለመክፍት ያመች ዘንድ ከመንግሥት በሊዝ በተረከበው 22 ሺህ ካሪ ሜትር ላይ የተለያዩ ሕንፃዎችን ለመገንባት የዲዛይን ስራ ተጠናቆና የመሠረት ድንጋይ በብፁዕ አባታችን በአቡነ ቀሌምንጦስ ተጥሎ ግንባታውን ለማስጀመር በዝግጅት ላይ ነው፡፡ ግንባታው ከተጠናቀቀ በኋላ የተለያዩ መንፈሳዊ ኮሌጆችን ያቀፈ የቤተክርስቲኗ ከፍተኛ ተቋም እንደሚሆን ይታመናል፡፡


Abune Basilios Image


Abune Basilios Image

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መሠረትን እናጽና!